am_tw/bible/kt/body.md

1.6 KiB

አካል

“አካል” ቃል በቃል የሰው ወይም የእንስሳ ሥጋ ማለት ነው። ይህ ቃል አንድን ነገር ወይም በአንድ ቡድን ውስጥ ያሉ ግለ ሰቦችን ለማመልከትም ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

  • ቃል በቃል ሲወሰድ “አካል” የሞተ ሰው ወይም እንስሳን ይመለከታል። አንዳንዴ “የሞተ አካል” ወይም፣ “ሬሳ” ያመለክታል።
  • የመጨረዓው የፋሲካ ራት ላይ ኢየሱስ፣ “ይህ ሥጋዬ ነው” በማለት ሲናገር፣ ለኃጢአታቸው ክፍያ ለመሆን. “የሚቆረሰውን” (የሚገደለውን) ሥጋዊ አካሉን ማመልከቱ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያኖች እንደ አንድ ቡድን፣ “የክርስቶስ አካል” ተብለው ተጠርተዋል።
  • የሰው አካል ብዙ ክፍሎች እንዳሉት ሁሉ፣ “የክርስቶስ አካል” ብዙ ግለ ሰብ አባሎች አሉት።
  • በአንድነት እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለእርሱ ክብር እንዲሆን ለማገዝ እያንዳንዱ አማኝ የክርስቶስ አካል ውስጥ የራሱ የሆነ ተግባር አለው።
  • ኢየሱስ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች፣ “አካል ራስ (መሪ)” ተብሎአል። የአንድ ሰው ራስ አካሉ ምን ማድረግ እንዳለበት እንደሚናገር ሁሉ፣ እንደ “አካሉ” ብልቶች ክርስቲያኖችን የሚመራና አቅጣጫ የሚያስይዝ ኢየሱስ ነው።