am_tw/bible/kt/blasphemy.md

1.1 KiB

ስድብ፣ ተሰደበ

መጽሐፍ ቁስ ውስጥ፣ “ስድብ” እግዚአብሔርንና ሰውን በጣም በሚያንቋሽሽ መንገድ መናገርግን ያመለክታል። አንድን ሰው፣ “መስደብ” ሰዎች ሐሰት የሆነ መጥፎ ነገር እንዲያስቡ በዚያ ሰው ላይ ክፉ ነገር መናገር ማለት ነው።

  • ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔርን መሳደብ ሲባል እርሱን ማማት ወይም እርሱን በተመለከተ እውነት ያልሆነ ነገርን በመናገር መሳደብን ወይም እርሱን በማያስከብር ሁኔታ ውስጥ መኖርን ያመለክታል።
  • አንድ ሰው እግዚአብሔር ነኝ ቢል ወይም ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ሌላ እግዚአብሔር እንዳለ ቢናገር ያ ሰው ተሳድቦአል።
  • አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች ሰዎችን ስለ መሰደብ የሚያመለክት ከሆነ ይህን “ሐሜት” በማለት ተርጕመውታል።