am_tw/bible/other/yeast.md

1.3 KiB

እርሾ፣ የቦካ

እርሾ ሊጥ ኩፍ እንዲል የሚያደርግ ነገር ነው። እርሾ የገባበት ሊጥ የቦካ ይባላል።

  • በጥንት ዘመን ሊጥ እንዲቦካ ወይም ኩፍ እንዲል ከተፈለገ ለጥቂት ቀኖች መቀመጥ ነበረበት። የሚቀጥለው ሊጥ እንዲቦካ ለማድረግ በፊት ከነበረው ሊጥ ጥቂት ተወስዶ እንዲቀላቀል ይደረጋል።
  • እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ ሊጡ እስኪቦካ ድረስ ለመጠበቅ ጊዜ አልነበራቸውም፤ ስለዚህ ካልቦካ ሊጥ የተጋገረ እንፈራ ይዘው ነበር ጉዞ የጀመሩት። ለዚህ መታሰቢያ እንዲሆን በየዓመቱ አይሁድ የፋሲካን በዓል ሲያከብሩ ያልቦካ እንጀራ ይበላሉ።
  • ኀጢአት በሰው ሕይወት እንደሚስፋፋና ሌሎች ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ፣ “እርሾ” በሚለው ቃል ይጠቀማል። ይህ ሐሰተኛ ትምህርትንም ይመለከታል።
  • “እርሾ” የእግዚአብሔር መንግሥት ከአንዱ ሰው ወደ ሌላው እንዴት እንደሚተላለፍ ለማመልከት አዎንታዊ በሆነ መልኩም ጥቅም ላይ ውሏል።