1006 B
1006 B
የተጻፈ
“እንደ ተጻፈ” ወይም፣ “የተጻፈው” የተሰኙት ቃሎች አዲስ ኪዳን ውስጥ ተደጋግመው ጥቅም ላይ ውለዋል፣ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክቱት በዕብራውያን ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉ ትእዛዞች ወይም ትንቢቶች ነው።
- አንዳንዴ፣ “እንደ ተጻፈ” የሚለው የሚያመለክተው በሙሴ ሕግ ውስጥ የተጻፉ ነገሮችን ነው።
- ሌላ ጊዜ ደግሞ፣ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት አንዱን ለመጥቀስ ነው።
- ይህም፣ “በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ” ወይም፣ “ከብዙ ዘመን በፊት ነቢያት እንደ ጻፉት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
- ሌላ ጊዜ ደግሞ፣ “እንደ ተጻፈ” የሚለውን መተርጎምና ያ ምን ማለት እንደ ሆነ በግርጌ ማስታወሻ ማመልከት ሌላው አማራጭ ሊሆን ይችላል።