am_tw/bible/other/winnow.md

1.3 KiB

ማበራየት፣ ማበጠር

“ማበራየት” እና፣ “ማበጠር” ለምግብ የሚሆነውን እህል ከማይፈልጉ ነገሮች መለየት ማለት ነው። ስሞችን መለየትን ወይም መክፈልን አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁለቱም ቃሎች በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ውለዋል።

  • ማበራየት ነፋስ ገለባውን እንዲወስደው እህሉንና ገለባውን ወደ አየር በመበተን እህልን ከማይፈለገው ገለባ መለየት ማለት ነው።
  • “ማበጠር” የሚባለው ድንጋይን ጠጠርን የመሳሰሉ የማይፈለጉ ነገሮች ከእህሉ እንዲለዩ የተበራየውን እህል በወንፊት ማበጠር ማለት ነው።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ጻድቃንን ከኀጢአተኞች የሚለይ አስቸጋሪ ሁኔታን ለማመልከት፣ “መበራየት” እና፣ “ማበጠር” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ ውለዋል።
  • እርሱንም ሆነ ሌሎች ደቀ መዛሙርት በእምነታቸው ፈተና እንደሚገጥማቸው ለማመልከት አንድ ጊዜ ኢየሱስ፣ “ማበጠር” በሚለው ቃል ተጠቅሞ ነበር።