am_tw/bible/other/well.md

1.6 KiB

ጉድጓድ፣ ውሃ ማጠራቀሚያ

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን፣ “ጉድጓድ” እና “ውሃ መያዣ” ሁለት የተለያዩ የውሃ መገኛ ቦታዎችን ነበር የሚያመለክተው።

  • ጉድጓድ መሬት ውስጥ ያለው ውሃ ወጥቶ እንዲጠራቀምበት ጠለቅ ተደርጎ የሚቆፈር ጉድጓድ ነው።
  • ውሃ መያዣም ጠላት ተደርጎ የተቆፈረ ጉድጓድ ሲሆን የዝናብ ውሃ ለማጠራቀም ያገልግላል።
  • ብዙውን ጊዜ ውሃ መያዣ ከዐለት ተፈልፍሎ የተሠራ ሲሆን፣ ውሃው እንዳይባክን በመክደኛ ይከደን ነበር። “ውሃ መያዝ የማይችል” የሚባለው መክደኛው ተሰንጥቆ ውሃ የሚያሰርግ ሲሆን ነው።
  • ውሃ መያዣዎች 6 ሜትር ጥልቀትና 1 ሜትር ስፋት ይኖራቸዋል።
  • ለሰዎችም ሆነ ለእንስሳት ውሃ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ የውሃ ጉድጓድ አጠቃቀምን አስመልክቶ ብዙ ፀብና ግጭት ይፈጠራል።
  • እነርሱ ውስጥ ምንም ያልተፈለገ ነገር እንዳይገባ ጉድጓድም ሆነ የውሃ መያዣ በትልቅ ድንጋይ ይገጠማሉ። ብዙውን ጊዜ ውሃ ቀድቶ ለማውጣት ባልዲ የታሰረበት ገመድ ይኖራል።
  • ዮሴፍና ኤርምያስ ላይ ከሆነው እንደሚታየው አንዳንድ ጊዜ የደረቁ የውሃ መያዣዎች እንደ እስር ቤት ያገለግሉ ነበር።