1.5 KiB
1.5 KiB
ንጹሕ ያልሆነ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ንሑሕ ያልሆነ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር የሚያመለክተው ሕዝቡ ሊነካው፣ ሊበላው ወይም መሥዋዕት ሊያቀርበው እንደማይገባው እግዚአብሔር የተናገረለት ነገርን ነው።
- እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የትኛው እንስሳ ንጹሕ፣ የትኛው እንስሳ ንጹሕ እንዳልሆነ መመሪያ ሰጥቷል። ንጹሕ ያልሆኑ እንስሳት እንዲበሉ ወይም መሥዋዕት እንዲቀርቡ አልተፈቀደም።
- አንዳንድ ዐይነት የቆዳ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከዚያ እስኪፈወሱ ድረስ ንጹሕ እንዳልሆኑ ይቆጠሩ ነበር።
- እስራኤላውያን ንጹሕ ያልሆነ ነገር ከነኩ ለተወሰነ ወቅት እነርሱ ራሳቸው ንጹሕ እንዳልሆኑ ይቆጠሩ ነበር።
- ንጹሕ ያልሆነ ነገርን ባለመንካትና ባለመብላት ለእግዚአብሔር መታዘዝ እስራኤላውያንን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ያደርጋቸው ነበር።
- ይህ አካላዊና ሥርዓታዊ ንጹሕ አለመሆን፣ የግብረ ገባዊ ርኩሰት ምሳሌ ነበር።
- በሌላ ምሳሌያዊ አነጋገር፣ “ንጹሕ ያልሆነ/ርኩስ” መንፈስ ክፉ መንፈስን ያመለክታል።