803 B
803 B
አሥሩ ትእዛዞች
እግዚአብሔር ለሙሴ እስራኤል ሊታዘዟቸው የሚገባ ብዙ ትእዛዞች ሰጥቶታል። ከእነዚህ ትእዛዞች አሥሩን በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፏቸዋል።
- አሥሩ ትእዛዞች እስራኤላውያን እግዚአብሔርን እንዲወዱና እንዲያመልኩት፣ ሌሎች ሰዎችንም እንዲወዱ ለመርዳት የታሰቡ ልዩ ትእዛዞች ናቸው።
- እነዚህ ትእዛዞች እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ኪዳን አካል ናቸው። እግዚአብሔር እንዲያደርጉ ለሰጣቸው ትእዛዝ ከታዘዙ እግዚአብሔርን መውደዳቸውንና የእርሱ መሆናቸውን ያሳያሉ።