1.1 KiB
1.1 KiB
በግ፣ አውራ፣ እንስት በግ
በግ አካሉ ላይ የሱፍ መሥሪያ ጠጉር ያለው መጠነኛ ቁመት ያለው ባለአራት እግር እንስሳ ነው። ወንዱ በግ አውራ ሲባል ሴቷ እንስት በግ ትባላለች
- እስራኤላውያን አብዛኛውን ጊዜ መሥዋዕት የሚያቀርቡት በግ በተለይም ወንዱንና ከግልገል ከፍ ያለውን በግ ነበር
- ሰዎች የበጎችን ሥጋ ይመገባሉ፤ ጠጉራቸውን ሱፍና ሌሎች ነገሮችን ለመሥራት ይጠቀሙበታል
- በግ ሌሎችን የሚያምኑ፣ ደካማና ድንጉጦች ናቸው። በቀላሉ ከቦታቸው የሚኮበልሉ ናቸው። በትክክለኛው አቅጣጫ የሚመራቸው፣ የሚከለከልላቸውና ምግብ፣ ውሃና መጠለያ የሚያዘጋጅላቸው እረኛ ያስፈልጋቸዋል
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች የእግዚአብሔር እረኝነት በሚያስፈልጋቸው በጎች ተመስለዋል