1.3 KiB
1.3 KiB
መፈለግ፣ ፈለገ
“መፈለግ” አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር መሻት ማለት ነው። ኅላፊው ግሥ፣ “ፈለገ” የሚለው ነው። አንድን ነገር ለማድረግ “አጥብቆ መሞከር” ወይም፣ “ከባድ ጥረት ማድረግ” ማለትም ይሆናል
- አንድን ዕድል፣ “መፈለግ” ወይም፣ “መሻት” አንድን ነገር ለማድረግ፣ “ጊዜ ለማግኘት መሞከር” ማለት ነው
- “ያህዌን መፈለግ” ማለት፣ “ያህዌን ለማወቅና ለእርሱ መታዘዝን ለመማር ጊዜንና ጉልበትን መስጠት” ማለት ነው
- “ከለላ መፈለግ” – “ከአደጋ የሚከልላችሁን ሰው ወይም ቦታ አጥብቆ መፈለግ” ማለት ነው
- “ፍትሕ መፈለግ” – “ሰዎች እውነተኛና ትክክለኛ ፍርድ ሲያገኙ ለማየት ማንኛውንም ጥረት ማድረግ” ማለት ነው
- “እውነትን መፈለግ” – “እውነቱ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ማድረግ” ማለት ነው
- “ሞገስ መፈለግ” – “መወደድን መፈለግ” ወይም፣ “አንድ ሰው እንዲረዳችሁ መፈለግ” ማለት ነው