927 B
927 B
ሳንደል
ሳንደል ከእግር ታችኛው ክፍልና ከቁርጭምጭሚት ጋር በክር የሚታሰር ሰለል ያለ ጫማ ነው። ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ይጠቀሙበት ነበር
- ሳንደል ንብረት መሸጥን የመሳሰሉ ሕጋዊ ውሎችን ለማጽናት ጥቅም ላይ ይውል ነበር። (ሩት 4፥7)፣ እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ አንደኛው ወገን ሳንደሉን በማውለቅ ለሌላው ወገን ይሰጠው ነበር
- ጫማን ወይም ሳንደልን ማውለቅ በተለይ በእግዚአብሔር ፊት ከሆነ የአክብሮትና የመገዛት ምልክት ነው
- ዮሐንስ የኢየሱስን ጫማ ክር ለመፍታት እንኳ ብቁ እንዳልሆነ ተናግሮአል፤ በዚያ ዘመን ይህን ማድረግ በጣም ዝቅ ያለ አገልጋይ ወይም ባርያ ሥራ ነበር