am_tw/bible/other/prostrate.md

1.6 KiB

መደፋት

“መደፋት” የሚለው ቃል ፊትን ወደ መሬት በማድረግ መዘርጋት ማለት ነው። በድንገት በጣም ዝቅ ብሎ ማጎንበስ ማለት ነው።

  • አንድ ሰው ፊት፣ “መደፋት” ወይም፣ “ራስን መድፋት” በዚያ ሰው ፊት በድንገት ራስን በጣም ዝቅ በማድረግ ፊትን ወደ መሬት መድፋት ማለት ነው።
  • ብዙውን ጊዜ እንዲህ የሚሆነው አንዳች ተአምራዊ ነገር ከመሆኑ የተነሣ ድንጋቴ፣ መደንቅና ፍርሃት ሲኖር ነው። ፊቱ ለሚደፉለት ሰው ያለውን ክብርና አድናቆትም ያመለክታል።
  • መደፋት እግዚአብሔር የሚመለክበትም መንገድ ነው። አንድ ተአምር ሲያደርግ እንደ ታላቅ መምህር እርሱን ለማክበር በምስጋናና በአምልኮ ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያለ ምላሽ ይሰጡ ነበር።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መደፋት” የሚለውን ቃል፣ “ፊትን ወደ መሬት በማድረግ በጣም ዝቅ ብሎ ማጎንበስ” ወይም፣ “በፊቱ ፊትን ዝቅ አድርጎ ማምለክ” ወይም፣ “በመደነቅ ፊትን ወደ መሬት ዝቅ ማድረግ” ወይም፣ “ማምለክ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “ራሳችንን አንደፋም” የሚለው ሐረግ፣ “አናመልክም” ወይም፣ “በአምልኮ ፊታችንን ዝቅ አናደርግም” ወይም፣ “ዝቅ ብለን አናመልክም” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።