am_tw/bible/other/pillar.md

1.9 KiB

ዐምድ፣ ምሰሶ

“ዐምድ” ጣራ ወይም ሌላውን የሕንጻ ክፍል ደግፎ ለመያዝ የሚያገለግል ቀጥ ብሎ የሚቆም ነገር ነው። “ምሰሶ” የዐምድ ሌላ ስም ነው።

  • ከብሉይ ኪዳን እንደምንመለከተው ሳምሶን በፍልስጥኤማውያን በተያዘ ጊዜ ሕንጻውን ደግፈው የነበሩ ዐምዶች በመነቅነቅ ቤተ መቅደሳቸው እንዲፈርስ አድርጓል።
  • አንዳንዴ ዐምዱ የመቃብር ምልክት ወይም ይአንዳች ታሪካዊ ሁነት መታሰቢያ በመሆን ያገለግላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሕንጻዎችን የሚደግፉ ዐምዶች የሚሠሩት አብዛኛውን ጊዜ ቀጥ ብሎ ከወጣ አንድ ግንድ ወይም ድንጋይ ነበር።
  • ብዙውን ጊዜ የመታሰቢያ ዐምድ የሚሆነው አንድ ትልቅ ድንጋይ ወይም የተለያዩ ነገሮች ክምር ነበ።ር
  • አንዳንዴ፣ “ዐምድ” የሚለው ቃል ሐሰተኛ አምላክን ለማምለክ የሚያገለግል ምስል ማለትም ይሆናል። ሌላው መጠሪያው፣ “የተቀረጸ ምስል” ሲሆን፣ “ሐውልት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “ዐምድ” ቀጥ ብሎ የወጣ ነገር መጠሪያም ይሆናል፤ ለምሳሌ እስራኤል በምድረ በዳ ይጓዙ በነበረ ጊዜ በሌሊት ይመራቸው የነበረው፣ “የእሳት ዐምድ” ወይም የሎጥ ሚስት ዘወር ብላ ከተማዪቱን በመመልከትዋ፣ “የጨው ዐምድ” መሆንዋን የሚያመለክተውን ማየት ይቻላል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ ይህ ቃል፣ “ሐውልት” ወይም፣ “ደጋፊ ድንጋይ” ወይም፣ “መታሰቢያ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።