am_tw/bible/other/perverse.md

1.9 KiB

ጠማማ፣ የተጣመመ

“ጠማማ” ግብረ ገባዊ ወልጋዳነት ወይም ገዳዳነት ያለውን ሰው ወይም ተግባር ለሚመለከት ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው። “የተጣመመ” - ወልጋዳ ማለት ነው።

  • ጠማማ የሆነ ሰው ወይም ነገር መልካምና ትክክል ከሆነው የወጣ ማለት ነው።
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው ለእግዚአብሔር ባለ መታዘዝ እስራኤል የተጣመመ ሕይወት ኖረዋል። አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ የሆነው ሐሰተኛ አማልክትን በማምለካቸው ነበር።
  • ከእግዚአብሔር መለኪያ ወይም ባሕርይ የማይስማማ ማንኛውም ነገር ጠማማ ተብሎ ይጠራል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ “ጠማማ” የሚለውን ቃል ለመተርጎም የሚጠቅሙ መንገዶች፣ “ግብረ ገባዊ ገዳዳ የሆነ” ወይም፣ “የተበላሸ” ወይም፣ “ቀጥተኛ ከሆነው የእግዚአብሔር መንገድ የወጣ” የተሰኙት ሊሆኑ ይችላሉ።
  • “ጠማማ ንግግር” የሚለውን ቃል፣ “ክፉ መናገር” ወይም፣ “አሳሳች ንግግር” ወይም፣ “የማይረባ አነጋገር” በማለት መተርጎም ይቻላል።
  • ጠማማ ሕዝብ” የሚለውን ሐረግ፣ “ገዳዳ ሕዝብ” ወይም፣ “ከግብረ ገብ ውጪ የሆነ ሕዝብ” ወይም፣ “ዘወትር ለእግዚአብሔር የማይታዘዝ ሕዝብ” በማለት መተርጎም ይቻላል።
  • “የተጣመመ ተግባር” የሚለውን ሐረግ፣ “ክፉ ሥራ” ወይም፣ “ከእግዚአብሔር ትምህርት በወጣ መንገድ መኖር” በማለት መተርጎም ይቻላል።