929 B
929 B
ቤተ መንግሥት
“ቤተ መንግሥት” ከቤተሰቡና ከአገልጋዮቹ ጋር ንጉሥ የሚኖርበት ሕንፃ ወይም ቤት ማለት ነው።
- አዲስ ኪዳን እንደሚነግረን ሊቀካህናቱም የሚኖረው በቤተ መንግሥት ነበር።
- ቤተ መንግሥቶች በጣም ያጌጡ፣ ሕንፃዎቻቸው ያማሩና ውስጣቸው ያለው ዕቃም የተሟላ ነበር።
- የቤተመንግሥት ሕንፃዎችና ዕቃዎቻቸው ከድንጋይ ወይም ከእንጨት የተሠሩ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ በጣም ውድ በሆኑ እንጨቶች፣ ወርቅ ወይም የዝሆን ጥርስ ይለበጡ ነበር።
- አብዛኛውን ጊዜ በርካታ ሕንፃዎችና አደባባዮች በሚኖሩት ቤተ መንግሥት ውስጥ ሌሎች ብዙ ሰዎችም ይኖራሉ፤ እዚያም ይሠራሉ።