1.6 KiB
1.6 KiB
የበላይ ተመልካች
የበላይ ተማልካች የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የሌሎች ሰዎች መብትና ጥቅም መከበሩን የመቆጣጠር ሥራ በኅላፊነት የሚከታተል ሰው ነው።
- ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተመልካች የሚባለው በእርሱ ኅላፊነት ስር ያሉ ሠራተኞች ሥራቸውን በአግባቡ እየፈጸሙ መሆኑን የሚከታተል ሰው ነበር።
- አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል፣ የጥንት ቤተክርስቲያን መሪዎችን ለመመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። የእነርሱ ተግባር ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሲ ትምህርት ማግኘታቸውን ጨምሮ የአናኞችን መንፈሳዊ ጉዳይ በበላይነት መምራት ነበር።
- የበላይ ተመልካች የእርሱ፣ “መንጋ” የሆኑትን አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ አማኞች እንደሚጠብቅ እረኛ እንደሆነ ጳውሎስ ያመለክታል።
- እንደ እረኛ ሁሉ የበላይ ተመልካችም መንጋውን ይጠብቃል። አማኞችን ይመራል፣ መንፈሳዊ ትምህርትና ክፉ ተፅዕኖ ካላቸው ነገሮች ይጠብቃል።
- ኢየሱስም ዋናው የቤተክርስቲያን የበላይ ተመልካች ተብሏል።
- “የበላይ ተመልካች” – “ሽማግሌ” እና፣ “እረኛ/ፓስተር” የተሰኙት ቃሎች ተመሳሳይ መንፈሳዊ መሪዎችን የሚያመለክቱ የተለያዩ አገላልጾች እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል።