am_tw/bible/other/newcovenant.md

1.6 KiB
Raw Blame History

አዲስ ኪዳን

“አዲስ ኪዳን” የሚለው አገላለጽ የሚያመለክተው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕት በኩል እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገውን ስምምነት ወይም ውል ነው።

  • እግዚአብሔር የገባው፣ “አዲስ ኪዳን” “አዲስ ኪዳን” በመባል በሚታወቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ተብራርቶአል።
  • ይህ አዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ጋር ካደረገው፣ “አሮጌ” ወይም፣ “የቀድሞ” ኪዳን ጋር ይነጻጸራል።
  • ለሕዝቡ ኀጢአት ለዘላለም ፍጹም ቤዛ በሆነው በኢየሱስ መሥዋዕት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አዲሱ ኪዳን ከአሮጌው ይበልጣል። በአሮጌው ኪዳን ሲቀርቡ የነበሩ መሥዋዕቶች ይህን ማድረግ አልቻሉም።
  • አዲሱን ኪዳን በኢየሱስ በሚያምኑት ሰዎች ልብ ውስጥእግዚአብሔር ይጽፈዋል። ይህም ለእግዚአብሔር መታዘዝ እንዲፈልጉና የተቀደሰ አኗኗር ምኖር እንዲጀምሩ ያደርጋቸዋል።
  • በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር መንግሥቱን በዚህ ምድር ሲመሠርት አዲሱ ኪዳን ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር እንደ ነበረው ማንኛውም ነገር እንደ ገና መልካም ይሆናል።