am_tw/bible/other/memorialoffering.md

1.5 KiB

መታሰቢያ፣ የመታሰቢያ ቁርባን

መታሰቢያ የሚለው ቃል አንድ ሰው ወይም አንድ ሁኔታ እንዲታሰብ የሚያደርግ ተግባር ወይም ነገር ማለት ነው።

  • “የመታሰቢያ ቁርባንን” ወይም፣ “መታሰቢያ ክፍል” ወይም፣ “የመታሰቢያ ድንጋይ” ከሚሉት ማየት እንደሚቻለው ይህ ቃል አንዳች ነገርን እንዲያስታውሱ የሚያደርጉ ነገሮችን የሚያመለክት ቅጽል በመሆንም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • በብሉይ ኪዳን፣ “የመታሰቢያ ቁርባን” ይቀርብ የነበረው እግዚአብሔር ያደረገላቸውን እስራኤላውያን እንዲያስታውሱ ነበር።
  • ካህናት የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች የተቀረጸባቸው የመታሰቢያ ድንጋዮች ያሉበት ልዩ ልብስ እንዲለብሱ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። ምናልባትም እግዚአብሔር ምን ያህል ለእነርሱ ታማኝ መሆኑን እንዲያስታውሱ ለማድረግ ይሆናል።
  • ለድኾች ያደርግ ከነበረው ችሮታ የተነሣ ቆርኔሌዎስ የተባለውን ሰው እግዚአብሔር እንዳከበረ ከአዲስ ኪዳን እናነባለን። ይህ መልካም ሥራው በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ ሆነ።