ኀላፊ፣ ባለ ዐደራ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ኀላፊ” ወይም “ባለ ዐደራ” የሚለው የጌታውን ንብረትና የሥራ እንቅስቃሴን በተመለከተ ሙሉ ኀላፊነት የተሰጠውን አገልጋይ ለማመልከት ነው።
- ባለ አደራ በጣም ትልቅ ኀላፊነት የተሰጠው ሰው ሲሆን፣ ሌሎች አገልጋዮችን የመቆጣጠርንም ሥራ ይጨምራል።
- ባለ አደራ ከሚለው ይልቅ፣ “ኀላፊ” የሚለው ይበልጥ በዘመኑ የተለመደ ቃል ነው፤ ሁለቱም የሚያመለክቱት የሌላው ሰው ተግባራዊ ጉዳዮችን ማስተዳደርን ነው።