ዝቅተኛ፣ ዝቅተኝነት
“ዝቅተኛ” እና፣ “ዝቅተኝነት” የተሰኙት ቃሎች ድህነትን ወይም ዝቅ ያሉ ማንነትና ደረጃን ያመለክታሉ።
- ኢየሱስ ሰው ወደ መሆንና ባርያ ወደ መሆን ደረጃ ድረስ ራሱን ዝቅ አደረገ።
- እርሱ የተወለደው ቤተ መንግሥት ሳይሆን የከብቶች ማደሪያ በረት ውስጥ ስለ ነበር ልደቱም በጣም ዝቅተኛ ነበር።
- ዝቅተኛ ለሚለው ሌላው ቃል፣ “ትሑት” የሚለው ሊሆን ይችላል።
- ዝቅተኛ ዝንባሌ የትዕቢተኝነት ተቃራኒ ነው።