1.7 KiB
1.7 KiB
ብርሃን
መጽሐፍ ቅዱስ “ብርሃን” የሚለውን ቃል በተለያዩ ምሳሌያዊ ገለጻዎች ይጠቀምበታል። ብዙውን ጊዜ ጻድቃን፣ ቅድስናንና እውነትን ለማመልከት እንደ ተለዋጭ ዘይቤ ያገለግላል።
- የእግዚአብሔርን እውነተኛ መልእክት ወደ ዓለም ማምጣቱንና ሕዝቡንም ከጨለማና ከኀጢአት እንደሚያድን ለማመልከት ኢየሱስ፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” አለ።
- ክርስቲያኖች “በብርሃን እንዲመላለሱ” ታዝዘዋል፤ ያም ማለት እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ መኖርና ክፋትን ማስወገድ አለባቸው ማለት ነው።
- ሐዋርያው ዮሐንስ፣ “እግዚአብሔር ብርሃኝ” እንደ ሆነና በእርሱ ጨለማ እንደሌለ ጽፏል።
- ብርሃንና ጨለማ ፍጹም ተቃራኒ ናቸው። ጨለማ ምንም ዐይነት ብርሃን ያለ መኖር ማለት ነው።
- እርሱ፣ “የዓለም ብርሃን” እንደ ሆነና ተከታዮቹም እግዚአብሔር ምንኛ ታላቅ መሆኑን በሚያሳይ መንገድ እየኖሩ በዓለም ውስጥ እንደ ብርሃን ማንጸባረቅ እንደሌለባቸው ኢየሱስ ተናግሮአል።
- “በብርሃን መመላለስ” መልካምና ትክክል የሆነውን በማድረግ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ መኖርን ይወክላል። በጨለማ መመላለስ በእግዚአብሔር ላይ እያመፁ መኖርንና ክፉ ነገሮችን ማድረግን ይወክላል።