ለምጽ፣ ለምጻም
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን፣ “ለምጽ” የተለያዩ የቆዳ በሽታዎችን ያመለክት ነበር። አንድ ሰው ከእነዚህ የቆዳ በሽታዎች በአንዱ ከተያዘ ርኵስ ተብሎ ይቆጠር ነበር።
- “ለምጻም” የሚባለው ለምጽ ያለበት ሰው ነው።
- “ለምጻም” በለምጽ የተያዘ ሰው ወይም የአካል ክፍልን የሚገልጽ ቃል ነው።
- መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ለምጻሞች ከሌሎች ሰዎች ተለይተው ከሰፈር ወይም ከከተማ ውጪ እንዲኖሩ ይደረግ ነበር።