መብራት መያዣ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መብራት መያዣ” ክፍሉ ውስጥ ሁሉ እንዲያበራ መብራቱ የሚቀመጥበት ከእንጨት ወይም ከብረት የተሠራ ዕቃ ነው።
- ለቤተ መቅደሱ የሚሠራው ልዩ መብራት መያዣ ሰባት መብራቶች የሚይዙበት ቦታ ነበሩት።
- መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን መብራት ብዙውን ጊዜ የወይራ ዘይት ወይም ስብ የያዘ ከሸክላ የተሠራ ዕቃ ሲሆን ሲቀጣጠል ብርሃን የሚሰጥ ክር ወይም ፈትል ውስጡ ይደረግ ነበር።