1.0 KiB
1.0 KiB
ደስታ፣ ደስተኛ
ደስታ የደስታ ስሜት ወይም ከእግዚአብሔር የሚመጣ ጥልቅ ርካታ ነው። ከዚሁ ጋር ታያያዥ የሆነው፣ “ደስተኛ” የሚለው ቃል በጣም ደስ የተሰኘ ሰውን ያመለክታል።
- እያለፈበት ያለው መልካም መሆኑን በተመለከተ ጥልቅ ግንዛቤ ሲኖረው አንድ ሰው ደስታ ይሰማዋል።
- ለሰዎች እውነተኛ ደስታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው።
- ደስ ለመሰኘት የግድ ደስ የሚል አካባቢ ወይም ሁኔታ ውስጥ መሆን የለብንም በሕይወታቸው በጣም አስቸጋሪ ነገሮች እየተፈፀሙ እንኳ እግዚአብሔር ለሰዎች ደስታ መስጠት ይችላል።
- አንዳንዴ ቤቶችን ወይም ከተሞችን የመሳሰሉ ነገሮች ደስ የሚያሰኙ ተብለዋል። እንዲህም ማለት እዚያ የሚኖሩ ሰዎች ደስተኞች ናቸው ማለት ነው።