1.2 KiB
1.2 KiB
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ፣ “ቤት” ጥቅም ላይ የዋለው በምሳሌያዊ መልኩ ነው።
- አንዳንዴ፣ አንድ ቤት ውስጥ አብሮ የሚኖሩ ሰዎችን የምያመለልክት፣ “ቤተ ሰብ” እንደ ማለት ይሆናል።
- ብዙ ጊዜ፣ “ቤት” የአንድን ሰው ቅድመ አባቶች፣ ዘሮች ወይም ዘመዶች ያመለክታል፤ ለምሳሌ፣ “የዳዊት ቤት” እንደሚለው።
- “የእግዚአብሔር ቤት” እና፣ “የያህዌ ቤት” የተሰኘው ሐረግ መገናኛውን ድንኳን ወይም ቤተ መቅደስን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። በጠቅላላው እግዚአብሔር ያለበትን ወይም የሚኖርበትን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
- ዕብራውያን 3 ላይ፣ “የእግዚአብሔር ቤት” ሲል እንደ ተለዋጭ ዘይቤ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወይም የበለጠ ጠቅለል ባለ መልኩ መላውን የእስራኤልን ሕዝብ ወይም በሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት ያሉ ነገዶችን ለይቶ ማመልከቱ ነው።