926 B
926 B
ፈረስ
ፈረስ ግዙፍ ባለ አራት እግር እንስሳ ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በአብዛኛው ለእርሻ ሥራና ለሰዎች መጓጓዣ ያገለግል ነበር።
- አንዳንድ ፈረሶች ሰረገላና ጋሪ ለመጎተት ሲያገለግሉ፣ ሌሎች ሰዎችን በመሸከም ያገለግሉ ነበር።
- ወደ ተፈለገው አቅጣጫ ፈረሶችን መምራት እንዲቻል አፋቸው ውስጥ ልጓም ይገባል።
- መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በአመዛኙ በጦርነት ጊዜ ካላቸው ጠቀሜታ የተነሣ ፈረሶች እንደ ትልቅ ሀብት የባለጠጋነት መለኪያ ይቆጠሩ ነበር። ለምሳሌ ንጉሥ ሰሎሞን አንድ ሺህ ፈረሶች ነበሩት።
- ፈረስ የሚመስሉ እንስሳት አህያና በቅሎ ናቸው።