1.2 KiB
1.2 KiB
ቀንድ፣ ቀንዶች
ቀንዶች ላምና በሬ፣ በጎችና ፍየሎች የመሳሰሉ እንስሳት ራስ ላይ የሚበቅል ቋሚና ሹል ነገር ነው። ብርታትን፣ ኀይልን፣ ሥልጣንና ንጉሥነትን ለማመልከትም “ቀንድ” በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
- የበግ ቀንድ በአንዳንድ ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ጊዜ የሚነፋውን፣ “ሸፋር” የተሰኙ የሙዚቃ መሣሪያ መሥሪያ ይሆናል።
- ከናስ የተሠራው የዕጣን መሠዊያ ላይ በአራቱም አቅጣጫ የቀንድ ቅርጽ ያለው ነገር እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። እነዚህ ነገሮች “ቀንዶች” ተብለው ቢጠሩም ትክክለኛ የእንስሳት ቀንዶች አልነበሩም።
- ውሃ ወይም ዘይት ለመያዣ የሚያገለግለው ቀንድ መሰል ብልቃጥ አንዳንዴ፣ “ቀንድ” ተብሎ ይጠራል። የዘይት ብልቃጥ ሳሙኤል ዳዊት ላይ እንዳደረገው አንድን ንጉሥ ለመቀባት ያገለግላል።