1021 B
1021 B
ከፍታ ቦታዎች
“ከፍታ ቦታዎች” የሚለው ሐረግ የጣዖት አምልኮ መሠዊያና ማምለኪያ ቤት የሚሠራባቸው ኮረብቶች ወይም ተራሮች ላይ ያሉ ቦታዎችን ያመለክታል።
- በእነዚህ ከፍታ ቦታዎች ለሐሰተኛ አማልክት መሠዊያዎች በመሥራት ብዙዎቹ የእስራኤል ንጉሦች እግዚአብሔርን በድለው ነበር። ይህም ሕዝቡ በከፍተኛ ደረጃ ጣዖት እንዲያመልኩ አደረገ።
- እግዚአብሔርን የሚፈራ ንጉሥ በእስራኤል በነገሠ ጊዜ ሁሉ ከፍታ ቦታዎችን ያስወግድና ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ነበር።
- ይሁን እንጂ፣ ከእነዚህ መልካም ንጉሦች አንዳንዶቹ ቸልተኛ ነበሩ፤ መላው የእስራኤል ሕዝብ ጣዖት ማምለኩን እንዲቀጥል ምክንያት የሆኑትን ከፍታ ቦታዎች አላስወገዱም።