መፈወስ፣ ፈወሰ
መፈወስ የሰው ቁስል፣ ሕመም ወይም ዕዐይነ ስውርነትና የመሳሰሉ ጉድለቶች ከእንግዲህ እንዳይኖሩ ማደረግ ነው። ወይም የታመመውን ወይም ዐቅም ያጣውን ሰው እንደ ገና ጤነኛ ማድረግ ነው።
- የተፈወሰ ሰው ደኅና ሆኖአል ማለት ነው።
- ተፈጥሮአዊ ፈውስ የሚሆነው ቀስ በቀስ ነው።
- ብዙውን ጊዜ ተአምራዊ ፈውስ የሚሆነው አቅጽበት ነው፤ ለምሳሌ ጴጥሮስ ሽባውን ሰው ወዲያውኑ መራመድ እንዲችል እንዳደረገው።