am_tw/bible/other/head.md

1.8 KiB

ራስ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ራስ” በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞች አሉት።

  • ብዙውን ጊዜ ይህ ቃል ሰዎች ላይ ባለ ሥልጣን መሆንን ያመለክታል፤ ለምሳሌ፣ “በሕዝቦች ላይ ራስ አደረግኸኝ” እንደሚለው ይህ፣ “የሕዝቦች መሪ አደረግኸኝ” ወይም፣ “ሥልጣን ሰጠኸኝ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • ኢየሱስ፣ “የቤተ ክርስቲያን ራስ” ተብሏል። የሰው ራስ የሰውነት ብልቶቹን እንደሚምራና አቅጣጫ እንደሚያስይዝ ሁሉ ኢየሱስም “የአካሉን” ማለትም የቤተ ክርስቲያን ብልቶች (አባሎች) ይመራል፤ አቅጣጫ ያስይዛል።
  • ባል የሚስቱ ራስ ወይም ባለ ሥልጣን መሆኑን አዲስ ኪዳን ያስተምራል። ሚስቱንና ቤተሰቡ የመምራትና አቅጣጫ የማስያዝ ኀላፊነት ተሰጥቶታል።
  • “በራሱ ላይ ምላጭ አያልፍም” የሚለው አገላለጽ፣ “ጠጉሩ አይቆረጥም ወይም አይላጭም” ማለት ነው።
  • “ራስ” የአንድን ነገር ጅማሬ ወይም ምንጭ ሊያመለክትም ይችላል፤ ለምሳሌ፣ “የመንገዱ ራስ” እንደሚለው።
  • ሰውየውን ሽማግሌ ነው ለማለት የሰውየው “ራሱ ግራጫ ነው” ሲባል ራሱን ብቻ ሳይሆን ሙሉውን ሰው ይወክላል፤ “የዮሴፍ ራስ” ዮሴፍን ያመለክታል።
  • “ደማቸው በራሱ ላይ ይሁን” ሲባል ለእነርሱ ሞት ኀላፊነቱን ይወስዳል፤ በዚያም ምክንያት ይቀጣል ማለት ነው።