የወይን ፍሬ
ወይን ፍሬ የወይን ሐረጉ እዚህና እዚያ ተበታትነው የሚያድጉ ትናንሽ ክብ ፍሬዎች ናቸው። ወይን ጠጅ የሚሆነው እነዚህ ፍሬዎች ተጨምቀው ነው።
- ሰዎች የወይን እርሻቸው ውስጥ ወይን ይተክላሉ። ብዙውን ጊዜ ይህ የሚሆነው የወይን ግንዶችን መደዳውን በመትከል ነው።
- የወይን ፍሬዎች ብዙ ጊዜ ስለማይቆዩ ከበሰሉ በኋላ ለመብላት ሰዎች ያደርቋቸዋል። እነዚህ የደረቁት ወይኖች ዘቢብ ይባላሉ። ብሉይ ኪዳን ስለ ዘቢብ ጥፍጥፍ የሚለው አለው።