1.1 KiB
1.1 KiB
በኩር
“በኩር” የሚለው ቃል መጀመሪያ የሚወለደውን የሰውም ሆነ የእንስሳትን የመጀመሪያ ልጅ ነው።
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ “በኩር” የሚያመለክተው መጀመሪያ የሚወለድ ወንድ ልጅን ነው።
- መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የበኩር ልጅ ሌሎች ልጆች የሚያገኙትን የቤተሰብ ዕጥፍ የመውረስ መብት ነበረው።
- ብዙውን ጊዜ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚቀርበው መጀመሪያ የተወለደው እንስሳ ነበር።
- ይህ ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩም ጥቅም ላይ ይውላል። ለምሳሌ ከሌሎች ሕዝቦች የተለየ መብት ስለሰጣቸው የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔር በኩር ተብለው ተጠርተው ነበር።
- በሌሎች ሁሉ ላይ ባለው ሥልጣንና የበላይነት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስም “በኩር” ተብሏል።