852 B
852 B
የኅብረት መሥዋዕት፣ የሰላም መሥዋዕት
የኅብረት መሥዋዕት ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰላም መሥዋዕት ተብሎ ይጠራል። ተባዕት ወይም እንስት እንስሳ መሥዋዕት የሚቀርብበት ነው።
- ይህ መሥዋዕት ከሚቀርብበት ምክንያቶች ጥቂቶቹ፣ ስእለትን ለመፈጸም፣ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ውዳሴ ለማቅረብ፤
- የመሥዋዕቱ የተወሰነው ክፍል ለእግዚአብሔር ከቀረበ በኋላ የኅብረቱን መሥዋዕት ካህናቱ፣ መሥዋዕቱን ያመጣው ሰው እና ሌሎች እስራኤላውያን ይከፋፈሉታል።
- ከዚህ መሥዋዕት ጋር ያልቦካ እንጀራንም የሚያካትት አብሮ መብላትም ይኖራል።