1.0 KiB
1.0 KiB
በዓል
በዓል ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው በመመገብ የሚይሳልፉት ሁኔታ ሲሆን፣ እንዲህ የሚደረገው አንድን ሁኔታ አብሮ ለማክበር ሊሆን ይችላል። “በዓል ማድረግ” በልዩ አይነት ሁኔታ የተዘጋጀ ምግብ በብዛት መመገብን ያሳያል።
- አይሁዳውያን እንዲያከብሩ እግዚአብሔር ያዘዛቸው በዓሎች ብዙውን ጊዜ አብሮ ደስተኛ ጊዜ ማሳለፍንም ያካትታል።
- ነገሥታትና ሌሎች ሀብታሞችና ታዋቂ ሰዎች ብዙውን ጊዜ መብልና መጠጥ ለሰዎች የሚያቀርቡበት ግብዣ (በዓል) ያደርጋሉ።
- ስለጠፋው ልጅ በተነገረው ታሪክ ልጁ ወደቤቱ በተመለሰ ጊዜ አባትዮው የተለየ ግብዣ (በዓል) አድርጎ እንደነበረ እናያለን።
- አንዳንዴ ግብዣው ለጥቂት ቀኖች ወይም ከዚያም በላይ ሊቆይ ይችላል።