775 B
775 B
መታገሥ፣ ትዕግሥት (ጽናት)
መታገሥ ረጅም ጊዜ መቆየት ወይም አስቸጋሪ ነገርን መቋቋም ማለት ነው።
- የፈተና ጊዜ ሲመጣ ተስፋ ሳይቆርጡ ጸንቶ መቆም ማለትም ነው።
- “መታገሥ - “መቻል” – “በመከራና ስደት ውስጥ መጽናት” ማለት ነው።
- “እስከ መጨረሻ ጽኑ” በማለት ለክርስቲያኖች የተሰጠው ማበረታቻ ምንም እንኳ ያንን ማድረጋቸው ከባድ መከራ ሊያመጣባቸው ቢችልም ለኢየሱስ መታዘዝ እንደሚገባቸው ያሳስባቸዋል።
- “መከራን መታገሥ” ሲባል፣ “መከራን መለማመድ” ማለትም ነው።