1.3 KiB
1.3 KiB
ሽማግሌ
ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ሕዝብ መሐል መንፈሳዊና ተግባራዊ መሪነት ኀላፊነት ያላቸው መንፈሳዊ ማስተዋል ያላቸው ስሞች ናቸው።
- መጀመሪያ ላይ ይህ ቃል የተወሰደው ሽማግሌዎቹ የሚሆኑት በዕድሜያቸውና በሕይወት ልምዳቸው ከወጣቶች ይልቅ አስተዋይ የሆነ ስምች ስለ ነበሩ ነው።
- ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሽማግሌዎች ማኅበራዊ ፍትሕንና የሙሴ ሕግን በተመለከተ እስራኤላውያን በመምራት ያገለግሉ ነበር።
- አዲስ ኪዳን ውስጥ የአይሁድ ሽማግሌዎች ማኅበረ ሰባቸውንና በመምራትና ሕዝባቸውን በመዳኘት ቀጥለው ነበር።
- በጥንት ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያን ሽማግሌዎች በየአካባቢው በነበረ የአማኞች ጉባኤ መንፈሳዊ አመራር ይሰጡ ነበር።
- መንፈሳዊ ማስተዋል ያላቸው ወጣቶችም የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ይሆኑ ነበር።
- ይህ ቃል፣ “በዕድሜ የገፉ ሰዎች” ወይም፣ “ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩ መንፈሳዊ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።