አለመታዘዝ፣ የማይታዘዝ
“አለመታዘዝ” ሥልጣን ላይ ያለ ሰው ትእዛዝን ወይም መመሪያን አለመቀበል ማለት ነው። ይህን የሚያደርግ ሰው የማይታዘዝ ይባላል።
- ማድረግ የሌለበትን የሚያደርግ ሰው ታዛዥ አይደለም።
- የታዘዙትን አለማድረግ አለመታዘዝ ነው።
- ሆን ብሎ የታዘዘውን የማያደርግ ዐመፀኛ ሰው፣ “የማይታዘዝ” ይባላል።
- “የማይታዘዙ ሰዎች” የሚለውን፣ “ዐመፀኞች” ወይም፣ “እግዚአብሔር ያዘዘውን የማያደርጉ” ብሎ መተርጎም ይቻላል።