1.7 KiB
1.7 KiB
የተጠላ፣ መጥላት
“የተጠላ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይወደድና የተናቀ ነገር ነው። አንድን ነገር “መጥላት” ያንን ነገር አጥብቆ አለመውደድ ማለት ነው።
- መጽሐፍ ቅዱስ ክፉን ስለ መጥላት ደጋግሞ ይናገራል። ይህም ክፉን አለመውደድና ክፉን መጽሐፍ ማለት ነው።
- ሐሰተኛ አማልክትን የሚያመልኩ ሰዎች የሚያደርጉትን ክፉ ሥራ አስመልክቶ ሲናገር እግዚአብሔር፣ “የተጠላ” በሚለው ቃል ተጠቅሟል።
- ጎረቤቶቻቸው የነበሩ አገሮች ያደርጉ የነበረውን ኃጢአትና ርኵሰት እንዲጠሉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዞአል።
- ቅጥ ያጣ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን እግዚአብሔር፣ “የተጠላ” ብሎታል።
- ጥንቆላ፣ መተትና ሕፃናትን መሥዋዕት ማድረግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ናቸው።
- “መጥላት” የሚለውን ቃል፣ “አለመውደድ” ወይም፣ “መጸየፍ” ወይም፣ “መናቅ” ብሎ መተርጎም ይቻላል።
- እርሱ ራሱ፣ “ርኵስ” ያላቸውንና ለምግብነት መዋል እንደሌለባቸው የተናገረላቸው አንዳንድ እንስሳት፣ እንዲጠሉ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። ይህ፣ “በጣም መጸለይ” ወይም፣ “ማስወገድ” ወይም፣ “ተቀባይነት እንደሌለው ነገር መቁጠር” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።