1.4 KiB
1.4 KiB
ማርከስ፣ መርከስ
“ማርከስ” እና፣ “መርከስ” የተሰኙት ቃሎች መበከልን ወይም በከፍተኛ ደረጃ መቆሸሽን ያመለክታሉ። አንድ ነገር ከአካላዊ፣ ከግብረ ገባዊ ወይም ከሃይማኖታዊ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ርኵስ ተብሎ ሊጠራ ይችላል።
- እርሱ፣ “ርኵስ” ወይም “ያልተቀደሰ” ያለውን በመብላት ወይም በመንካት ራሳቸውን እንዳያረክሱ እግዚአብሔር እስራኤላይውያንን አስጠንቅቆ ነበር።
- የሞቱ አካሎችና ተላላፊ በሽታዎችን የመሳሰሉ ነገሮችን እግዚአብሔር ርኵሳን ብሏቸዋል፤ እነርሱን የሚነኩ ሰዎች ይረክሳሉ።
- ከዝሙት ኃጢአት እንዲርቁ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዞአል። ይህ ኃጢአት ያረክሳችዋል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጡ ያደርጓቸዋል።
- የተወሰኑ ሥርዓቶችን በመፈጸም እንደ ገና ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ለጊዜውም ቢሆን ሰውን የሚያረክሱ ከአካል የሚወጡ ነገሮች ነበር።
- አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድን ሰው በእውነት የሚያረክሱት ኃጢአተኛ ዐሳብና ተግባር እንደ ሆኑ ኢየሱስ አስተምሮአል።