1.2 KiB
1.2 KiB
ማሳሳት፣ መሳት፣ ስሕተት፣ አሳሳች
“ማሳሳት” እውነት ያልሆነ ነገር እንዲታመን ማድረግ ነው። ሌሎችን የማሳሳት ተግባር “ማሳት” ይባላል።
- “ስሕተት” የተሰኘው ሌላ ቃልም እንዲሁ እውነት ያለሆነ ነገር እንዲታመን ማድረግ ነው።
- ሐሰትን እንዲያምኑ የሚያደርግ ሰው “አሳሳች” ነው። ለምሳሌ ሰይጣን፣ “አሳሳች” ተብሎ ተጠርቷል። እርሱ የሚቆጣጠራቸው ክፉ መናፍስትም አሳሳቾች ናቸው።
- እውነተኛ ያልሆነ ሰው፣ ተግባር ወይም መልእክት፣ “አሳሳች” ተብሎ ሊጠራ ይችላል።
- “ማሳት” እና፣ “ስሕተት” የተሰኙት ቃሎች ተመሳሳይ ትርጕም ቢኖራቸውም ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ በተመለከተ መጠነኛ ልዩነት አላቸው።
- “አሳሳች” እና “አሳች” የተሰኙት ገላጭ ቃሎች ተመሳሳይ ትርጕም አላቸው፤ በተመሳሳይ ዐውድ ጥቅም ላይ ይውላሉ።