am_tw/bible/other/crown.md

2.8 KiB
Raw Blame History

አክሊል፣ አክሊል መድፋት (መጫን)

አክሊል ንጉሦችና ልዕልታትን የመሳሰሉ መሪዎች ራሳቸው ላይ የሚያደርጉት ክብ ቅርጽ ያለው ጌጥ ነበር። አክሊል መድፋት አንድ ሰው ራስ ላይ አክሊል ማኖር ማለት ሲሆን፣ በምሳሌያዊ ትርጕሙ፣ “ማክበርን” ያመለክታል።

  • ብዙውን ጊዜ አክሊል የሚሠራው ከወርቅ ወይም ከብር ሲሆን የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮች ፈርጥ ይኖሩታል።
  • አክሊል የነገሥታትን ሥልጣንና ሀብት ያመለክታል።
  • በንጽጽር ሮማውያን ኢየሱስ ራስ ላይ ያኖሩት ከእሾክ ቅርንጫፎች የተሠራ አክሊል እርሱን ለመጉዳትና በእርሱ ለማፌዝ ታስቦ የተደረገ ነበር።
  • በጥንት ዘመን በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ያሸነፉ ሰዎች ከወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የተሠራ አክሊል ይሸለሙ ነበር። በሁለተኛው የጢሞቴዎስ መልእክቱ ሐዋርያው ጳውሎስ የጠቀሰው እንዲህ አይነቱን አክሊል ነበር።
  • በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “አክሊል መድፋት (መጫን)” ያንን ሰው ማክበር ማለት ነው። ለእርሱ ስንታዘዝና እርሱን ስናመሰግን እግዚአብሔርን እናከብራለን። ይህ እርሱ ላይ አክሊል የማኖርና ንጉሥነቱን የመቀበል ያህል ነው።
  • ጳውሎስ አማኝ ወገኖችን፣ “የደስታዬ አክሊል”ይላቸዋል። እዚህ ላይ “አክሊል” የሚለውን ቃል የተጠቀመው እነዚያ አማኞች በታማኝነት እግዚአብሔርን ከማገልገላቸው የተነሣ በእነርሱ ምን ያህል ደስ እንደ ተሰኘና ክብር እንደ ተሰማው በሚያመልክት ምሳሌያዊ መልኩ ነው።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል፣ “አክሊል” “ዋጋ” ወይም፣ “ክብር” ወይም፣ “ሽልማት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል፣ “አክሊል መድፋት (መጫን)” ማክበር ወይም መሸለም ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • አንድ ሰው አክሊል ካገኘ፣ “ራሱ ላይ አክሊል ተደረገ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • “ክብርና ግርማ ተቀዳጀ” የተሰኘው አገላለጽ፣ “ክብርና ግርማ ተሰጠው” ወይም፣ “ክብርና ግርማ ተቀበለ”፣ “ክብርና ግርማ ለበሰ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።