1.1 KiB
1.1 KiB
ምክር፣ መካሪ፣ አማካሪ
ምክር ማለት አንድ ሰው ማስተዋል ያለበት ውሳኔ እንዲያደርግ ተገቢውን ሐሳብ መስጠት ማለት ነው። መልካም “መካሪ” ወይም፣ “አማካሪ” ሰዎች ትክክልኛ ምርጫ ማድረግ እንዲችሉ አስፈላጊ ሐሳብ ይሰጣል።
- ብዙ ጊዜ ነገሥታት የሕዝቡን ሕይወት የሚነኩ አስፈላጊ ነገሮችን በተመለከተ ትክክለኛ ውሳኔ እንዲያደርጉ የሚረዷቸው አማካሪዎች ነበሯቸው።
- አንዳንድ የሚሰጠው ምክር መልካም ላይሆን ይችላል። ተገቢ ያልሀነ አንድ ርምጃ እንዲወሰድ ወይም ራሱንና ሕዝቡን የሚጎዳ ዐዋጅ እንዲያወጣ ክፉ መካሪዎች ንጉሡን ያሳስታሉ።
- እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “ምክር” ወይም “መካሪ” የተሰኙ ቃሎች፣ “ውሳኔ ለማድረግ የሚጠቅም ሐሳብ” ወይም፣ “ጠቃሚ አስተያየት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።