1.3 KiB
1.3 KiB
ሸንጎ፣ ምክር
ሸንጎ በጣም አስፈላጊ ጉዳዮችን በተመለከት ለመወያየት፣ ምክር ለመስጠትና ውሳኔ ለማሳለፍ የተሰበሰቡ ሰዎች ማለት ነው።
- ሕገ ነክ የሆኑ ጕዳዮችን አስመልክቶ ውሳኔ ማሳለፍን ከመሳሰሉ ዓላማዎች አንጻር ብዙ ጊዜ ሸንጎ የሚቋቋመው ዕውቅና ባለውና ዘላቂነት ባለው መልኩ ነው።
- ከፍ ያለ ሥልጣን የነበረው የአይሁድ ሸንጎ ሳንሔድሪን በመባል የሚታወቀው ነበር። ሳንሔድሪን ሊቃነ ካህናትን፣ ሽማግሎዎችን፣ ጸሐፍትን፣ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም የመሳሰሉ አይሁድ መሪዎችን የሚያካትት 70 አባሎች ነበሩት።
- ወንጌልን በማስተማሩ የታሰረ ጊዜ ሐዋርያው ጳውሎስ የሮማውያን ሸንጎ ፊት ቀርቦ ነበር።
- እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “ሸንጎ” – “ሕጋዊ ጉባኤ” ወይም፣ “የፖለቲካዊ ጉባኤ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
- “ሸንጎ ውስጥ መሆን” ታላላቅ ነገሮችን መወሰን የሚችል ስብሰባ ውስጥ መሆን ማለት ነው።