1.0 KiB
1.0 KiB
መጨረስ
ቃል በቃል ሲወሰድ እስኪያልቅ ድረስ አንድን ነገር መጠቀም ማለት ሲሆን በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም ይኖሩታል።
- መጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መጨረስ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ነገሮችን ወይም ሰዎችን ማጥፋት ይመለከታል።
- እሳት ነገሮችን እንዲጨርስ (እንደሚበላ) ሲነገር ዐመድ እስከሆኑ ድረስ እቃጥሎ ይፈጃቸዋል ማለት ነው።
- እግዚአብሔር፣ “የሚባላ እሳት” ተብሏል፤ ይህ ኃጢአት ላይ ያለውን ቊጣ የሚገልጽ ነው። ቊጣው በንስሐ ይማይመለሱ ኃጢአተኛ ላይ ከባድ ቅጣት ያመጣል።
- ምግብ መጨረስ እስኪያልቅ ድረስ መብላት ወይም መጠጣት ማለት ነው።
- “ምድሪቱን በላ” የሚለው ሐረግ፣ “ምድሪቱን አጠፋ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።