943 B
943 B
የካህናት አለቆች
ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ የካህናት አለቆች ከፍ ያለ ሥልጣን የነበራቸው የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ነበሩ።
- የካህናት አለቆች ቤተ መቅደስ ውስጥ በሚደረገው የአምልኮ አገልግሎት ማንኛውም ነገር ላይ ኃላፊነት ነበራቸው፤ ለቤተ መቅደስ የሚሰጠውን ገንዘብ የሚቆጣጠሩትም እነርሱ ነበሩ።
- ከተራዎቹ ካህናት የበለጠ ደረጃና ሥልጣን ነበራቸው። ከእነርሱ የሚበልጥ ሥልጣን የነበረው ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር።
- የካህናት አለቆች ከኢየሱስ ዋነኛ ጠላቶች ጥቂቶቹ ሲሆኑ፣ እርሱን እንዲይዙና እንዲገድሉት ሮማውያን መሪዎች ላይ ከባድ ተጽዕኖ ያደረጉ እነርሱ ነበሩ።