1.0 KiB
1.0 KiB
መደምሰስ፣ ደመሰሰ
“መደምሰስ” እና፣ “ደመሰሰ” የሚለው ቃል ሰዎችን ወይም ነገሮችን ጨርሶ ማስወገድ ወይም ማጥፋትን የሚያመለክት ፈሊጣዊ ቃል ነው።
- እነዚህ ፈሊጣዊ ቃሎች፣ ይቅር በማለትና ጨርሶ ማሰብ ባለ መፈለግ፣ የሰዎችን ኃጢአት “ሲደመስስ” ቀና በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
- ብዙዎን ጊዜ በኃጢአታቸው ምክንያት ሰዎችን በማጥፋት እግዚአብሔር “ሲደመስስ” ወይም፣ “ሲያስወግድ” ያለውን ሁኔታ ለማመልከት በአሉታዊ መልካም ጥቅም ላይ ይውላል።
- መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ስም ከእግዚአብሔር ሕይወት መጽሐፍ “መደምሰሱን” ወይም፣ “መጥፋቱን” በተመለከተ ይናገራል፤ እንዲህ ሲሆን ሰውየው የዘላለም ሕይወት አያገኝም ማለት ነው።