am_tw/bible/other/biblicaltimeyear.md

1.7 KiB
Raw Blame History

የመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ፤ ዓመት

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃል በቃል ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “ዓመት” 354 ቀኖች የያዙ ጊዜን ያመለክታል። ይህ ጨረቃ በምድር ዙሪያ ለመዞር የሚወስድባትን ጊዜ መጸት እንደማይደርገው እንደ ጨረቃ አቆጣጠር ነው።

  • በዚህ ዘመን ጥቅም ላይ የዋለው የፀሐይ ዑደትን መሠረት ያደረገው አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 12 ወሮች ያሉት 365 ቀኖች አሉት፤ ይህም ምድር በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ ማለት ነው።
  • በሁለቱም ቀን አቆጣጠር አንድ ዓመት 12 ወሮች አሉት። ይሁን እንጂ የጨረቃ አቆጣጠር ከፀሐይ አቆጣጠር ከዓመት 11 ቀኖች ስለሚቀንስ የጨረቃ ቀን አቆጣጠር ላይ አንድ ተጨማሪ ወር ይኖረዋል። ይህም ሁለቱም የቀን አቆጣጠሮች እርስ በርስ የሚመጣጠን ጊዜ እንዲኖራቸው ይረዳል።
  • አንድ ልዩ ሁኔታ የተፈጸመበትን ጊዜ እንዲሁ በደፈናው ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ዓመት” የሚለው ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መንገድም ጥቅም ላይ ይውላል። ይህን የሚመለከቱ ምሳሌዎች፣ “የያህዌ ዓመት” ወይም፣ በረሐብ ዘመን” ወይም፣ “የተወደደችው የጌታ ዓመት” የተሰኙትም ያካትታሉ። በዚህ ዐውድ መሠረት፣ “ዓመት” “ጊዜ” ወይም፣ “ወቅት” ወይም፣ “ዘመን” ተብሎ መተርጎም ይችላል።