am_tw/bible/other/biblicaltimemonth.md

1.5 KiB

የመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ ወር

“ወር” ሲባል አራት ሳምንት ገደማ ያለው ወቅ ነው። እንደምንጠቀምበት የጊዜ አቆጣጠር (በጨረቃ ወይም በፀሐይ) መሠረት አንድ ወር ውስጥ ያሉ ቀኖች ሊለያዩ ይችላሉ።

  • በጨረቃ ቀን አቆጣጠር የእያንዳንዱ ወር ርዝማኔ ጨረቃ በመሬት ዙሪያ ለመዞር እንደሚወስድበት ጊዜ መጠን (ማለት 29 ቀን) ይወሰናል። በዚህ አቆጣጠር በዓመት ውስጥ 12 ወይም 13 ወሮች ይኖራሉ።
  • “አዲስ ጨረቃ” ወይም ብርማ ብርሃን ያለበት የጨረቃዋ ገጽታ ጅማሬ በጨረቃ አቆጣጠር የምንጠቀም ከሆነ የእያንዳንዱ ወር ጅማሬ ይሆናል።
  • እስራኤላውያን ይጠቀሙ የነበሩት በጨረቃ አቆጣጠር ስለ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ወሮች ስም በሙሉ የጨረቃ አቆጣጠርን መሠረት ያደረጉ ናቸው።
  • በዚህ ዘመን ጥቅም ላይ የዋለው የፀሐይ አቆጣጠር መሬት በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ ላይ (365 ቀን ገደማ) የተመሠረተ ነው። በዚህ አቆጣጠር መሠረት ዓመቱ ሁሌም በአሥራ ሁለት ወሮች ይከፈላል፤ የየወሮቹ ርዝመት ከ28 እስከ 31 ቀኖች ገደብ ይወሰናል።