803 B
803 B
ድብ
ድብ ጥቁር ቡናማ ጠጉርና ጠንካራ ጥርሶችና ጥፍሮች ያሉት ባለአራት እግር ግዙፍ እንስሳ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ድብ በእስራኤል በብዛት ይገኝ ነበር
- እነዚህ አራዊት የሚገኙት ጫካዎች ውስጥና ተራራማ አካባቢዎች ነበር፤ ዓሶችን፥ ጥቃቅን ነፍሳትንና ተክሎችን ይመገባሉ
- በብሉይ ኪዳን ድብ የብርታትና ጥንካሬ ምሳሌ ተደርጎ ይቀርባል
- በጎች ይጠብቅ በነበረ ጊዜ እረኛው ዳዊት ከድብ ጋር ታግሎ አሸንፎ ነበር
- ሁለት ድቦች ከጫካ መጥተው ኤልሳዕ ላይ ያላገጡ በርካታ ልጆችን ገደሉ