913 B
913 B
ጢሮስ
ጢሮስ በአሁኑ ዘመን ሊባኖስ በሚባለው ሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ ላይ የነበረች ጥንታዊ የከነዓናውያን ከተማ ናት። የከተማዋ አንድ ክፍል ከባሕሩ ዳርቻ አንድ ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ካለው ደሴት ጋር ይያያዛል።
- የጢሮስ ከተማ እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ከመምጣታቸው በፊት ነበረች። ሁሌም የአረማውያን ከተማ ነበረች።
- ከነበረችበት ቦታና ከተፈጥሮ ሀብቷ የተነሣ ጢሮስ ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ሀብታም ከተማ ነበረች።
- የጢሮስ ሕዝብ በምግባረ ብልሹነታቸው ይታወቃሉ።
- ብዙ ጊዜ ጢሮስ አጠገቧ ካለችው ጥንታዊት ከተማ ሲዶና ጋር ትያያዛለች።